=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
![]() ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ! ![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። |
---|
- የመጨረሻው የአሏህ መልእክተኛ የነብይነት አዋጅ
- ሶላት
- የስብከት ጅማሮ
- አረመኔዎች በነብዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ያደረጉት ዘመቻ
- በብሄራዊ በአላት ያደረጔቸው ስብከቶች
- የቁረይሾች ጥላቻ
- ቢላል(ረ.ዐ)
- የቀደምት ሙስሊሞች ወደ አቢሲኒያ(ኢትዮዺያ) ያደረጉት ስደት
- የሐምዛ(ረ.ዐ) ኢስላምን መቀበል
- የኡመር(ረ.ዐ) ኢስላምን መቀበል
- የአቡጧሊብ እና የኸድጃ(ረ.ዐ) እልፈተ ሂወት
- በጧኢፍ የተካሄደው ስብከት
- እስልምና በያጥሪብ
- ሚዕራጅ
- ሙስሊሞች ከዑመር(ረ.ዐ) ጋር ወደ መዲና ያደረጉት ስደት
ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) 40 ዓመት በሞላቸው ጊዜ በ5ኛው ረቢዑል አወል የመላዕኮች አለቃ የሆነው ሩሁል አሚን ጅብሪል(ዐ.ሰ) ረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ የመጨረሻው ነብይ አድርጐ ሊያውጅ ከመለኮታዊ ትዕዛዝ ጋር ወደ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) መጣ። በዚያን ጊዜ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በሂራ ዋሻ ውስጥ ዱአ እያደረጉ ነበር። ጅብሪልም እንዲህ አለ: ሙሐመድ ሆይ! መልካም የምስራች አለህ፤ አንተ የአሏህ መልዕክተኛ ነህ። እኔ ጅብሪል ነኝ። በጌታህ ስም አንብብ አሏቸው። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ምንም ነገር ለማንበብ እንደማይችሉና እንዳልተማሩ ነገሩት። ጅብሪል(ዐ.ሰ) አጥበብቆ እቅፍ አደረጋቸው። ደጋግሞ እንዲህ ካደረጋቸው ቡኋላ ወደ ቤታቸው መጡና አልጋቸው ላይ ተኙ። ወዲያውኑ ትኩሳት ፣ ብርድብርድ ፣ ፍርሃት ይሰማቸው ጀመር።
ይህን ተከትሎ ኸድጃ(ረ.ዐ) ልብስ እንድታለብሳቸው ጠየቇት። ትንሽ ከታገሰላቸው ብኋላ እንዲህ እንዲህ አይነት አጋጣሚ አጋጠመኝ ብለው በነገሯት ጊዜ የአጐታቸው ልጅ ወደሆነው ዋርቃ የኖፍል ልጅ ወሰደቻቸው። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሙሉ ክስተቱን ተረኩለት። ይህን ከሰማ ቡኋላ ለሙሳ(ዐ.ሰ) እንደወረደው ያለ ተመሳሳይ ጅብሪል እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ አለ።
ከጥቂት ቀናት ቡኋላ ወደ ሂራ ዋሻ አቀኑና የመጀመሪያውን የቁርአን ወህይ ማለትም አምስቶቹ የሱራ አል-አቅ አናቅፅቶች ተገለፁላቸው። እነዚህ 5 አናቅፅቶች በኢስላም የማንበብ መለኮታዊ ጥቅምን የሚያሳዩ አናቅፅቶች ናቸው።
--<({አል-ቁርአን 96:1-5})>--
(1) አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
(2) ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
(3) አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
(4) ያ ሰውን በብርዕ ያስተማረ፡፡
(5) ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
ጅብሪል(ዐ.ሰ) ነብዩን(ሰ.ዐ.ወ) ከሂራ ዋሻ ከተራራው ስር ወሰዳቸውና ጅብሪል(ዐ.ሰ) ራሱ ውዱእ አደርጐ አሳያቸው። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ልክ እንደ ጅብሪል(ዐ.ሰ) በተመሳሳይ መንገድ ውዱእ አደረጉ። ጅብሪል(ዐ.ሰ) ኢማም ሆኖ ሶላት አብረው ሰገዱ።
ከጅብሪል(ዐ.ሰ) ጋር የመጀመሪያ ሶላት ከሰገዱ ብኋላ ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤታቸው ተመልሰው ውድ ሚስታቸውን ኸድጃን መስበክ ጀመሩ። ይች ሴት የመጀመሪያዋ የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊም ሚስት ሆነች። ኢስላምን እንደተቀበለች ሶላቷን መስገድ ጀመረች። አልይ(ረ.ዐ) የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የአጐታቸው ልጅ ፣ አቡበክር ሲዲቅ(ረ.ዐ) ሁሉም በመጀመሪያው ቀን ኢስላምን ተቀበሉ። የነሱ ወደ ኢስላም መግባት የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ታላቅነት ፣ ቅድስና ፣ ደግነትቸውንና መልካምነታቸውን ያረጋገጠ ነበር።
በመቀጠልም አሏህ በሱራ አል-ሒጀር ላይ በግልፅ ይሰብኩ ዘንድ ደነገገባቸው። በመጀመሪያ ደረጃ ቤተሰባቸውንና ወዳጅ ዘመዳቸውን ወደ ኢስላም ይጣሩ ዘንድ በሱረቱል አሹራ 214 ላይ አሏህ አዘዛቸው።
የሰውልጆች የሁል ጊዜም አርአያ ፣ ተምሳሌት የሆኑት የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ ይህ ነው። የአረመኔዎችን ማህበራዊ ክፋት ፣ ሃጢያት ፣ ጣኦት አምላኪነትንና የአሏህን አንድነት ስላስተማሩ የመካ ሙሽሪኮች አምርረው በመቃወም በጣም ከባድና የከፋ ዘመቻቸውን በነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ከፈቱ። በቻሉት አቅም በተለያዩ ጊዚያት ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) አወገዙ ፣ ተሳደቡ። ሙሐመድ በጅኒዎች የተለከፈ እብድ ነው አሉ። ሙሐመድ ጠንቇይ ፣ ድግምተኛ ፣ ገጣሚ ነው ሲሉም ተሳደቡ።
ይህ ሁሉ ይሁንእንጂ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በፅናት የኢስላምን መልዕክት ለሁሉም የሰው ልጆች ማድረሳቸውን ቀጠሉ። በእያንዳንዱ ስብሰባ ፣ በእያንዳንዱ በአል ፣ በእያንዳንዱ አውራጐዳና ፣ በእያንዳንዱ የእግር መንገድ የአሏህን አንድነትን በህዝባቸው ላይ ያሰርፁ ጀመር።
ከእምነተ ቢስነት ፣ ከዝሙት ፣ ከጣኦት አምላኪነት ፣ ሴት ልጆችን በሂወት መቅበርን እና ቁማርተኝነትን ከለከሏቸው።
የአከዝ ፣ የቢጅኒህ እና የዚልማህዝ ባአሎች በአረቢያ ውስጥ በጣም የታወቁ በአላት ሲሆኑ ራቅ ካለ ቦታ ያሉ ሰዎች ሳይቀሩ በነዚህ ባአላት ይገኛሉ። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በነዚህ ባአላት ይገኙና መለኮታዊ ወደ ሆነው የሰው ልጆች የተፈጥሮ ሃይማኖትና ወደ አሏህ አንድነት ሰዎችን ይጣራሉ። እንደዚህ አይነቱ የስብሰባ ንግግረቸው ቅን የሆኑ ትንሽ የሙስሊሞች ጀመአ እንዲፈጠር ምክኒያት ሆነ። አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ቁረይሾችን ይሰብኩ ዘንድ አመላከታቸው።
የቀረበላቸውን መለኮታዊ እውነታ በመመልከት እምነተ ቢስነታቸውንና ጣኦት አምላኪነታቸውን ለመተው እጅግ በጣም የእፍረትና የውርደት ስሜት ተሰምቷቸው መንገዶቹን ሁሉ ሊዘጉባቸው አሴሩ። በመጀመሪያ ደረጃ ቀላል የሆኑ መሰናክሎችን እንዲጋፈጡ በማድረግ የጀመሩ ሲሆን እያሉ እያሉ ግን ለከፋ ስቃይ ዳረጔቸው። አዲሶቹን ሙስሊሞች ወደ ጥንት ሃይማኖታቸው ለመመለስ ሲሉ ጠንካራ የተጋድሎ እንቅስቃሴ ጀመሩባቸው።
ቢላል(ረ.ዐ) ሐባሻዊ ሲሆን የኡመያ ቢን ኸውፍ ባሪያ ነው። ቢላል እስልምናን መቀበሉን ሲያውቅ አሳማሚ ጭቆናና ስቃይ አደረሰበት። ነገርግን ኢስላም ከልቡ ስለገባ ለዚህ ሁሉ ግፍና ስቃይ ቦታ አልሰጠውም። ይልቁንስ በመለኮታዊ ፍቅር ስለተነደፈ ሲገረፍ "አሃድ" «አሏህ አንድ ነው።» የሚለውን መፈክር ጩኾ ያሰማ ነበር።
ለእስልምና እምነት እንዲህ አይነት ቅንነት ካሳየ ቡኋላ አቡበክር(ረ.ዐ) ከባርነት ነፃ የሚሆንበትን ያህል ዋጋ ከፍለው ከባርነት ነፃ አወጡት።
አረመኔዎች ሙስሊሞችን ማሰቃየታቸውን በቀጠሉ ጊዜ ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ለደህንነታቸው ሲሉ ወደ ኢትዮዺያ እንዲሰደዱ ፈቀዱላቸው። ከዚህ ፍቃድ ቡኋላ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው 12 ሙስሊም ወንዶችና 4 ሙስሊም ሴቶች በድቅድቅ ጨለማ የጅዳን ወደብ አቇርጠው ጉዟቸውን ወደ ኢትዮዺያ አደረጉ። ኡስማን ቢን አፋን(ረ.ዐ) ከሚስቱ ሩቅያ(የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ልጅ)ና ጃእፈር ጠያር(ረ.ዐ) የዚህ ጉዞ መሪዎች ነበሩ።
ቁረይሾች ይህን ሲያውቁ ወደ ንጉስ ነጃሺ ቤተ-መንግስት መጡና እነዚህ ሰዎች የኛ ጐሳ አባሎች ናቸው። ከሃገራቸው አምልጠውነውና የመጡት ተመልሰው ለኛ ይሰጡን በማለት አቤቱታቸውን አቀረቡ። ለዚህም ጃእፈር(ረ.ዐ) እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ: አሏህ ምህረቱን በእኛ ላይ ችሮናል። ከመጨረሻው መለኮታዊ መጽሐፍ(ቁርአን) ጋር ነብዩ ሙሐመድን(ሰ.ዐ.ወ) ልኮልናል። ወደ አሏህ አንድነት ጠሩን ፣ ሃጢያትንና ጣኦት አምላኪነትን እንድንተው ፣ ለአሏህ እንድንሰግድ ፣ ምፅዋት እንድንሰጥ አስተማሩን። ማህበረሰባችነም ጠሉት። እስከሚችሉት ድረስም አሰቃዩን። እናም የትውልድ ሃገራችነን ትተን ተሰደድን አለ።
ንጉሱ ይህን በመስማት ቁርአን እንዲቀሩለት ፈለገ፤ ጃእፈር(ረ.ዐ) ከሱረቱል መርየም የተወሰኑ አናቅፅቶችን ቀራለት። ንጉሱ ማልቀስ ጀመረና እንዲህ አለ:- ኢሳ(ዐ.ሰ) እንደተነበየው አይነት ተመሳሳይ የአሏህ መልእክተኛ ነው። በሱ ዘመን በሂወት በመኖሬ ምስጋና ለአለማት ጌታ ይገባው አለ። እነዛም አረመኔዎች ሳይሳካላቸው ቀረና ወደቤታቸው ተመለሱ።
ከስድስት አመት የመካ ስብከት ቡኋላ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ከሶፋ ተተራራ ላይ ሆነው እየሰበኩያለ ዋናው የኢስላም ጠላት አቡጃህል እንደ ድንገት መጣ። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እውነተኛውን መለኮታዊ ራዕይ እየሰበኩ በማየቱ በጣም ተበሳጨና ሰደባቸው ፣ አጐሳቆላቸው ፣ እራሳቸውንም በድንጋይ ፈንክቶ አደማቸው። ሐምዛ(ረ.ዐ) ይህን ባወቀ ጊዜ ወደ አቡጃህል ጠጋአለና ጭንቅላቱን በቀስት መታው። ሐምዛ(ረ.ዐ) ለረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ቅርብ ሰው ነበር። ወደ እርሳቸው መጣና "አቡጃህልን ተበቀልኩላችሁ አልተደሰታችሁ ምንዴ" አላቸው። የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እስልምናን ስትቀበል እደሰታለሁ አሉት። ይህን ከሰማ ቡኋላ እስልምናን ተቀበለ። በፅኑ እምነቱ የሚታወቅ የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ጋሻ ሆነ።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
|
---|